Some things about Tedy Afro

 

ቴዲ ጥላቻን የሚያከስም የፍቅር ክትባት ነው!

This entry is part 24 of 27 in the series Teddy Afro

|ቴዲ በታሰረ በ415ኛው ቀን በዕለተ ቅዳሜ ተተየበ(ዳኛቸው ቢያድግኝ)|
የዘመናት የሕዝብ ብሶትን ያጨናገፈውና ሀሳዊ ድመሲዕ ሆኖ መጣሁላችሁ ብሎ በወርሀ ግንቦት የመጣብን የትግራይ ነጻ አውጪ እንደ ጠፉ ጎልያዶች ይጠፋል። እንደ ጥንብ ክርፋት በስብሶ ሲያልቅ ይረሳል። የፍቅር መንፈስ፣ የአንድነት ዝማሬ፣ የህብረት ፍካሬ ግን የትውልድ ዘመናትን እየተሸጋገረ በብርታት ላይ ጉልበት በእውቀት ላይ ብልህነት እያከለበት ይኖራል። ፍቅርን የዘከሩ ሰዎች ሊያልፉ ይችላሉ። ፍቅር ሲያልፍ ግን ዐለምም ይጠፋል። ሰማይና ምድር በፍቅር ተዘርግቶአልና!!

ፍቅር ከናፍቆት፣ ከመፈላለግ፣ ከመሰሰትና ከመሳሳት (መራራት) ጋር ይጣመራል። መለያየት የፍቅር ፈተና ነው። በአንድ ላይ ያለመሆን ለማሰብና ለመመዘን ያግዛል። እንደዋዛ የተመለከትነው ፍቅር ሲለየን ጣዕሙ ይታወቀናል፣ ዋጋው ይገባናል። በአለፍን በአገደምን ቁጥር ስለዚህ እንድናስብ እንገደዳለን። ፍቅርን መርሳት አይቻልም ከፍቅር ወደ ፍቅር መሸጋገር እንጂ!! ቴዲንም እንዲሁ በተከፋን ጊዜ እናስበዋለን፣ በደስታችንም ጊዜ አብሮን ነው። ቴዲ ቢኖር ኖር ይህን እንዲህ ያዜመው ነበር እያልን እንኳን የሚያደርገውን የማያደርገውን ሁሉ ለርሱ እንሰጠዋለን። የምንወደው ሰለወደደን ነው፣ አገሩን ስለወደደ ነው። ያከበርነው ከአገሬ ተለይቼ ህይወት የለኝም ስለአለን ነው። የኮራንበት እኛ ደፍረን ያልተነፈስነውን እርሱ በአደባባይ ሲያዜም ስለተመለከትነው ነው። ፍቅር ሰጥቶን ነው ፍቅራችንን የተቀበለ። ፍቅር ደግሞ መንፈስ፣ እሳቤ፣ ግንዛቤ ነው። በደም በስጋ በአጥንት ውስጥ ይገለጽ እንደሁ እንጂ አይኖርምና እግር ቆርጦ አይን ኣጥፍቶ ፍቅርን መቀነስ አይቻልም። ቴዲንም አስሮ ፍቅርን መንጠቅ አይቻልም። በአደባባይ ባያዜም በልባችን ዜማው ጠልቆ ገብቶአል። የዜማ ቃናችን ለሰሚ ባይመችም በግላችን እንናጎራጉራለን ለቴዲ ያለንን ፍቅር በሀሳብ በሚያገናኙን መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ እንነግረዋለን። አዝመራውን እያየ ፈገግ እንደሚል ገበሬ ከእስር ቤቱ ጉረኖ ውስጥ ሆኖ ልቡ የኩራት አታሞ ትደልቃለች። ተመስገን የፍቅር አዝመራዬ አማረልኝ እያለች።

የፍቅር አዝመራን በአረም መሙላት ደግሞ ወያኔያዊ ኢሕአዲጋዊ መንገድ ነው። ስልኩን፣ ፖስታውን፣ ኢንተርኔቱንና ሌሎች የመገናኛ መንገዶችን በማነቅ የፍቅርን እድገት መግታት እችላለሁ የሚል ግብዝ ነው። ግለሰቦችን ወደ እስር ቤት በመወርወር ፍቅርን ማገት ይቻላል ብለው የሚያስቡ ማሰቢያቸውን ማስፈተሽ ይገባቸዋል። ምክንያቱም ፍቅርን ከከተቡን በሁዋላ ቢታሰሩ ባይታሰሩ ጥላቻ ሊያሳውረን አይችልም። ክትባቱ ይሰራላ!! የግንኙነት አካላዊ መንገድ ብቻ ነው የሚደናቀፈው የፍቅር መንፈስ ግን ሁሌም የናፍቆት አዲስ መንገድ ይቀዳል። መናፈቅ መመኘት ነው። የተመኙትን ለማግኘት ደግሞ የሚከፈለው ሁሉ ይከፈላል።

ጥላቻ የፍቅር ተቃራኒ ነው። ከጥላቻ ፍቅር አይወለድም። ክፋትን ፈጽሞ ፍቅርን መሻት ግብዝነት ነው። በመከፋፈል፣ በማጣላትና ቅራኔን በማጋጋል ሊገኝ የሚችለው ጸብ፣ ጦርነት፣ እልቂትና ስር የሰደደ ጥላቻ ነው። ወያኔዎች ይህንን አምርተዋል፣ የክፋትን ትርፍ ዝቀውታል። እንኳን ለራሳቸው ቆምንልህ ለሚሉት የትግራይ ሕዝብም ክፋት እየሰፈሩለት ነው። ከየመንደሩ እየለቀሙ በስልጣን እያምነሸነሹ ጥርስ እያስነከሱባቸው ነው። የክፋት ጽዋው እየሞላ የሚፈስ እንባ ሲዥጎደጎድ ወያኔዎችን የምናመሳስለው ከእርኩስ መንፈስ ነው። እርኩስ መንፈስን ደግሞ አርባ ክንድ ያርቁታል። ስለዚህም የወያኔ መሪዎች ተደብቀውና ተሹለክልከው የአይጥ ኑሮ እንዲኖሩ ሆነዋል። ከዘሩት ክፋት ፍርሀትን አጭደው ሰው መሀል ሳይቆሙ ያጠፉዋቸው ነብሶች እንቅልፍ እየነሱአቸው ወደ ዲያቢሎስ አባታቸው መሄጃቸው ደርሶአል። የሚያቆዩት ክፋት ግን ብዙ የዋህና ሆድ አደሮችን ይዞ ይጠፋል። ሆድ አደር የወያኔ አገልጋዮች አንገታቸው ላይ ገመድ እንደታሰረላቸው በዳረጎት የሚኖሩ ውሾች ናቸው። እንቅስቃሴአቸው በታሰረላቸው የገመድ እርዝማኔ የሚለካ። ተነሱ ሲሉአቸው የሚነሱ ጃስ ሲሉአቸው የሚናከሱ ሰብዕናቸው የዘቀጠ እንደ ሰው በሁለት እግር የሚራመዱ እንስሶች ናቸው። እድሜና ተሞክሮ ካሉበት እልፍ ካላደረጋቸው እንዴት ብለን ሰው እንበላቸው? በእናታቸው ሞት እልል ብለው የሚጨፍሩ፣ በወገናቸው ሞት የእለት ጉርሳቸውን የሚያገኙ ከጥንብ አንሳ በምን ይለያሉ?? ጥንብ አንሳ ሌላ አውሬ የገደለውንና ከርሱ የተረፈውን ለመቦትረፍ የሚበር በራሱ ግዳይ የማይጥል የወፍ ዘር ነው። እንደ ውሎው ሁሉ መልከጥፉም ነው። እኒህ በፍርፋሪ የሚያድሩና አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ እንደዛገ እና የዶለዶመ ገጀራ ራቅ አርገው የሚጥሉአቸውን ሰዎች በአካል ከማየት ያፈቀሩትን እያሰቡ መልካሙን እየተመኙ መኖር ምንኛ ደስ ይላል።

እንደ ቴዲ ሁሉ ሰብዓዊ ፍጡርን እናክብር፣ ፍቅርን ዘርተን ደስታን እናምርት። ሰብዓዊ ክብራችንን ለሆዳችን ስንል ወደ እንስሳነት አናሳንሰው። አንድ ጊዜ ብቻ በምንኖርባት ዐለም ክብር አልባ ጦልጧላ ሆነን ለልጆቻችን የሚተርፍ ያደፈ ታሪክ አቆይተን አንለፍ። እንደ ተበጣጠቀ አሮጌ ጆንያ ሞልቶ የማይሞላ ከርስ የያዙ ሆዳሞችን የቴዲ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሕብረት መንፈስ ይጎብኛቸው።

የቴወድሮስ ካሣሁን የፍቅር መንፈስ አእምሮአችንን ልባችንን በደስታ ይሞላዋል። ፍቅር በአካልም ይገለጻል እንዳልኩት በሰለሜ ቅላጼ ክብ ሰርተን እጅ ለእጅ፣ ትከሻ ለትከሻ፣ ወገብ ለወገብ ተያይዘን እንወዛወዛለን። እንደ ቀስተደመና የሕብረቀለማት ፍንጥቅጣቂዎች በልዩነታችን መካከል ያለው አንድነታችን ደምቆ ያበራል። ቴዲ በእስር ቤትም እንኳ ሆኖ የዘራውን የፍቅር አዝመራ ማየት ይችል ዘንድ የሚጠራጠር ክትባቱን ያላገኘ ወይም ያልሰራለት ብቻ ነው። ለኛ ሰርቶልናልና ፍቅራችን ላምባዲና ሆኖ የተዘጉ ጉሮኖዎችን በሙሉ የተስፋ ብርሀን ይሙላባቸው።

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

 
Make a Free Website with Yola.